IMG_20230308_142120_195  
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመሬት አገልግሎቶች ላይ ጥሎት የነበረውን “ጊዜያዊ እግድ” አነሳ         
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙት 11 ክፍለ ከተሞች፤ ለሁለት ወር ገደማ ያህል ታግደው የቆዩ የመሬት አገልግሎቶችን በድጋሚ መስጠት መጀመራቸው ተገለጸ። የከተማዋ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፤ በመሬት አገልግሎቶች ላይ ተጥሎ የቆየውን “ጊዜያዊ እግድ” ከዛሬ ጀምሮ ማንሳቱን አስታውቋል።       
“ጊዜያዊ እግዱ” የተነሳው፤ የከተማዋ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ለአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ዛሬ ረቡዕ የካቲት 29፤ 2015 በጻፈው ደብዳቤ ነው። የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ፤ እግዱን መነሳቱን ለክፍለ ከተሞች በደብዳቤ ማሳወቃቸውን  ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።        
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በጥር ወር መጀመሪያ ላይ እግዱን ያስተላለፈው፤ ሁለት “መሰረታዊ መነሻዎችን” ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን ዶ/ር ቀነዓ ተናግረዋል። የቢሮ ኃላፊው በቀዳሚነት የጠቀሱት፤ በከተማዋ ውስጥ የሚታየውን “የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥነትን” ነው።        
የመሬት እግዱ ለመተላለፉ ሁለተኛው ምክንያት “መንግስት የጀመረው የጸረ ሙስና ትግል” መሆኑን ዶ/ር ቀነዓ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ይህንን የመንግስትን ዘመቻ ተከትሎ “መሬት፣ ንብረት እና የተለያዩ ሀብቶች አላግባብ እንዳይሸሹ” ለማድረግ እገዳው እንደተጣለ አስረድተዋል።       
* * ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ:-https://ethiopiainsider.com/2023/9949/




Share this post:

Related posts:
Right Property Agents company in Addis Ababa

Choosing Right Property Agents company in Addis Ababa is crucial for a successful real estate transaction. Here are five key points highlighting the importance of selecting our company: